1 ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ።
2 ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ በከፍታውም ሰላም አድራጊ ነው።
3 በውኑ ለሠራዊቶቹ ቍጥር አላቸውን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?
4 ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፥ ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል?
5 እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
6 ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!