Psa 3

? AI
1
አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።
2
ብዙ ሰዎች ነፍሴን። አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።
3
አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።
4
በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።
5
እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።
6
ከሚከብቡኝ ከአእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
7
ተነሥ፥ አቤቱ፤ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።
8
ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።
Global Bible Tools - Collaborative Bible translation platform