Psa 121

? AI
1
ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?
2
ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
3
እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም።
4
እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም።
5
እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል።
6
ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት።
7
እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።
8
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል።
Global Bible Tools - Collaborative Bible translation platform