Psa 124

? AI
1
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል።
2
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
3
ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤
4
በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤
5
በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።
6
ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ።
7
ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች። ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።
8
ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ስም ነው።
Global Bible Tools - Collaborative Bible translation platform