Psa 126

? AI
1
እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን።
2
በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን፥ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ። እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ።
3
እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገልን፥ ደስም አለን።
4
አቤቱ፥ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ።
5
በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ።
6
በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ።
Global Bible Tools - Collaborative Bible translation platform