Psa 129

? AI
1
እስራኤል። ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ ይበል፤
2
ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም።
3
ኃጢአተኞች በጀርባዬ ላይ መቱኝ፥ ኃጢአታቸውንም አስረዘሙአት።
4
እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ የኃጢአተኞችን አንገታቸውን ቈረጠ።
5
ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።
6
በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥
7
ለሚያጭደው እጁን፥ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ እቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።
8
በመንገዱም የሚያልፉ። የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን አይሉም።
Global Bible Tools - Collaborative Bible translation platform