Psa 134

? AI
1
እነሆ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ፥ በአምላካችን ቤት አደባባዬች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ።
2
በሌሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፥ እግዚአብሔርንም ባርኩ።
3
ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ።
Global Bible Tools - Collaborative Bible translation platform