Isa 4

? AI
1
በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች። የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ መሰደባችንንም አርቅ ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።
2
በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጥቋጥ ለጌጥና ለክብር ይሆናል፥ ከእስራኤልም ወገን ላመለጡ ሰዎች የምድሪቱን ፍሬ ለትምክሕትና ለውበት ይሆናል።
3
4
ጌታም የጽዮንን ቈነጃጅት እድፍ ባጠበ ጊዜ፥ የኢየሩሳሌምንም ደም በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስ ከመካከልዋ ባነጻ ጊዜ፥ በጽዮን የቀረ በኢየሩሳሌምም የተረፈ፥ በኢየሩሳሌም ለሕይወት የተጻፈ ሁሉ፥ ቅዱስ ይባላል።
5
እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራ ላይ ባለ ማደሪያ ሁሉ በጉባኤአቸውም ላይ በቀን ዳመናንና ጢስን በሌሊትም የሚቃጠለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብርም ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል።
6
በቀን ከሙቀት ለጥላ፥ ከዐውሎ ነፋስና ከዝናብም ለመጠጊያና ለመሸሸጊያ ጎጆ ይሆናል።
Global Bible Tools - Collaborative Bible translation platform